ጥ 21፡ የሶላት አርካን (ምሰሶዎች) ብዛት ስንት ነው?

መልስ - እንደሚከተለው አሥራ አራት ምሰሶዎች ናቸው፦

አንዱ፡- በተቻለ መጠን መቆም፤

ተክቢረቱል ኢሕራም፡ ይኸውም "አላሁ አክበር" ማለት ነው።

ፋቲሓ (አልሓምዱ)ን መቅራት፤

ጀርባን ለጥ አድርጎ በመዘርጋት እና ጭንቅላትንም በስትክክል አድርጎ ሩኩዕ ማድረግ (መጎንበስ)

ከሩኩእ መነሳት፤

ተስተካክሎ መቆም፤

ግንባርን፣ አፍንጫን፣ መዳፎችን፣ ሁለቱን ጉልበቶች እና የሁለቱን እግሮች ጣቶችን አስተካክሎ መሬት ላይ አድርጎ ሱጁድ ማድረግ፤

ከሱጁድ ቀና ማለት፤

በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ፤

የአቀማመጡ ሱናው፡ ቀኝ እግርን ቀጥ አድርጎ ተክሎ የእግርን ጣቶች ደግሞ ወደ ቂብላ ካቅጣጩ በኋላ በግራ እግር የውስጠኛው ክፍል ላይ መቀመጥ።

መረጋጋት: ይሀውም በእያንዳንዱ ምሰሶም ይሁን ድርጊት ላይ መረጋጋት፤

የመጨረሻው ተሸሁድ፤

ለተሸሁዱ መቀመጥ፤

ወደሁለቱም አቅጣጫ ማሰላመት: ይሀውም ሁለት ጊዜ፡- “አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ" እያሉ ነው።

ሩክኖችን - በጠቀስነው መልኩ - ማከታተል: ለምሳሌ ሆን ብሎ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ ቢያደርግ ሶላቱ ውድቅ ይሆናል። ተዘናግቶ ከሆነ ግን ተመልሶ ሩኩዕ ካደረገ በኋላ ከዚያም ሱጁድ ያደርጋል።